ማጣሪያ | EthioFactCheck: እውን ዶናልድ ትረምፕ ዶ/ር አብይን አሞግሰው White House ጠርተዋል?

 


አሉባልታው፡

“ሰበር [ዜና]
የአሜሪካው መሪ ትራንፕ ዶክተር አብይን አሞጋገሱ” – Lifë ፔጅ

“እጅግ ምርጥ የተከበረ መሪ ነው”
በማለት ዛሬ ስለ ጠ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ ፕሬዚደንት ትራንፕ በአስፈላጊው ሁኔታም እኛም ከጎኑ እንቆማለን በማለት አወደሱት…ቀጥለውም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት Donald Trump ከ abc News ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለ ዶ/ር አብይ ተጠይቀው የሚገርም ምላሽ ሰተዋል
” ህዝቡ የሚወደው ለሀገሩ ጥሩ ነገር ሊሰራ ቆርጦ የተነሳ ቆራጥ ብዙ መልካም ነገሮችን ለመስራትና ለማስተካከል የተዘጋጀ መሪ ነው ወድጀዋለሁ አምነውማለሁ አብረንም ለመስራት ተነጋግረናል ብለዋል ” – ክርስቲያኖች ቲዩብ (https://www.facebook.com/selmon.alemu.7965/videos/2118055488483401/)

Screen Shot 2018-06-19 at 10.09.55 PM.png

ብሎም “ወደ ዋይህት ሃውስ እጋብዘዋለሁ አለ…” ተብሎ በፌስቡክ እየተሰራጨ ይግኛል።


እውነት/ውሸት፦ ውሸት!


በቪዲዮው ላይ ዶናልድ ትራምፕ ስለ ሰሜን ኮሪያ መሪው ክም ጆንግ ኡን ያወራውን ሰዎች አቀነባብረውት ነው። ዶናልድ ትራምፕ ዶ/ር አብይን አያሞግስም፣ ወይም ወደ ዋይት ሀውስ አይጋብዝም ለማለት አይደለም፣ ወደፊት በዋይት ሃውስ ሊገናኙ ይችላሉ፤ነገር ግን በዚህ ቪድዮ ላይ ትረምፕ ስለ ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ ያለው ነገር ቢኖር፣ ከእሱና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት እንዳለው እና አብይን እየረዳውም እንደሆነ ብቻ ነው የተናገረው፣ የሚገርመው ደግሞ የስማቸው አጠራር ስለሚመሳሰል ነው እንጂ ትረምፕ ያወራው ጭራሽ ስለየኛው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ ሳይሆን ስለ ጃፓን ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢ(Abe)/አብይ (Prime Minster Shinzo Abe) ነበር::

ሌላው ውይይት በተለይ ወደ ዋይት ሃውስ መጋበዝ የተወራው ስለ ኪም ጆንግ ኡን ነበር። ያልተቀነባበረውን/ኦሪጅሉን ቪድዮ ከታች ሊንኩን ተጭናችሁ መመልከት ትችላላችሁ።
ኦሪጅናሉ ቪድዮ:-

– ይህ መጀመሪያ የተለጠፈው እአአ June 12, 2018 ሲሆን በሀበሻው ሚዲያ የተሰራጩት አሉባልታዎች ደግሞ ከJune 19 ጀምሮ ነበር::

ከጥሩ ማስረጃ ጋር የቀረበውን ቪዲዮ እዚህ ማየት ይቻላል፡
https://www.facebook.com/plugins/video.php?href=https%3A%2F%2Fwww.facebook.com%2Fhabeshasnetwork%2Fvideos%2F2093730467561423%2F&show_text=1&width=560

👉🏽 “ሳይገሉ ጎፈሬ ሳያስረግጡ ወሬ” ነውና፣ ለወደፊቱም አሉባልታዎችን በዚህ በEthioFactCheck | ማጣሪያ ላይ ያጣሩ (ያረጋግጡ) ወይም ይጠይቁ!

Leave a comment